Z Anointed Gold🕊

@CGFwow
Latest publications
Publication date:
16 Apr, 07:50
We're sons and daughters of the Light. No power emanating from the darkness shall defeat us. We're heavily protected. We're even the light of the world. We'll keep winning new souls to our Kingdom. We know who we're. We'll never expect approval from children of darkness. #Oracle
Pro Gold
👁 2 🔁 0 Publication date:
15 Apr, 06:27

እናመልክሃለን
እንወድሃለን
እናመሰግንሃለን
ኢየሱስ
ኢየሱስ
ኢየሱስ
ኢየሱስ
ኢየሱስ
ኢየሱስ
ኦ... ኢየሱስ!
Pro Gold
👁 4 🔁 0 Publication date:
13 Apr, 08:56
በማይታወቅ ልሳን መዘመር አደጋው ምኑጋ ነው?
(1ኛ ቆሮ. 14)
ሙዚቃ መናፍስት የሚረዱት ቋንቋ ነው። እንደየ ድምጻዊው ሰው እና እንደተሞዘቀው የሙዚቃ ዓይነት መንፈስ ቅዱስን አክብሮ አስከብሮ ያልፋል አለያም አጋንንትን ይስባል። አእምሯቸውንና ማስተዋላቸውን የሳቱ እብዶች ሙዚቃን ተረድተው ለምን እንደሚጨፍሩ አስባችሁ ታውቃላችሁ?
በባሕር ዓለም ወይም ጥልቁ ውስጥ ገብተው የዲያብሎስ ሰራተኞች የሆኑ ሁሉ አምላካቸውን ለማስደሰት ምንም ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ። በዚህ ዙሪያ ብዙ ምስጢሮች አሉ፤ ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን። አብዛኞቹ ዓለማዊ ሴት የሙዚቃ አርቲስቶች፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነፍሳትን ወደ ዲያብሎስ ለመሳብ ወጪያቸው ተሸፍኖ በቀጥታ የሚደገፉት በባሕር ዓለም መሪ በጨለማው መንግሥት ነው። የእነሱን ዘፈኖች ከዘፈናችሁ፣ አጋንንትን ወደ ሕይወታችሁና ወደ ቤታችሁ እየጋበዛችሁ መሆኑ ነው። በዚህ አጋጣሚ መዝሙር ስትሰሙ እረፍት የሚነሳችሁ ሰዎች ምን ያህል አጋንንት ህይወታችሁን እየተቆጣጠረው እንደሆነ መረዳት ትችላላችሁ። ጌታ ይገስጻቸው።
ከአጋንንት እስራት በመፍታት ዘርፍ የነጻነት አገልጋይ ከሆንክ ወይም መናፍስትን የመለየት ጸጋ ካለህ በሙዚቃ ክፍሉ ውስጥ ያሉ አብዛኞቹ (ዘማሪዎችም ሆኑ መሣሪያ ተጫዋቾች) በልዩ ልዩ አጋንንት የተያዙ መሆናቸውን አስረግጦ የሚነግርህ ነቢይ አያስፈልግህም። ለዚህ ነው በዚያ ክፍል ውስጥ (በዘፈኑና ሙዚቃ አለም) የዝሙት ርኩሰት እንደ ጄኔሬተር እና ነዳጅ አጥለቅላቂ የሆነው። ዝሙት የባሕር ዓለም(ማሪን ዎርልድ የምንለው) መንግሥትን ማሽኖች ያቀባብላል፣ ያንቀሳቅሳል። ኃይልን ከጨለማው ባሕር መንግሥት የተቀበሉ ሰዎች ስጦታቸውን በዝሙት መንፈስ ተዘፍዝፈው ማቀጣጠል ያለባቸው ለዚህ ነው።
በሚያሳዝን ሁኔታ የጸሎት ቡድን የሌላቸው አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት የሙዚቃ አገልጋዮችን ለመቅጠርና ለመክፈል በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ያወጣሉ። ተሳሳትኩ? ዋሸሁ? ከጸሎት ዝግጅት ይልቅ ለሙዚቃ ድግስ ትልቅ ግምት ቦታ ይሰጣሉ። የጨለማው ባሕር መንግሥት ከመድረክ እስከ ምእመናን መቀመጫ ወንበር ድረስ ቤተ ክርስቲያን የሚባሉትን ብዙ የአምልኮ ቤቶች የተቆጣጠረው ለዚህ ነው። ታስተውሉ ኖሮአል ፤ አማኞች ከልባቸው ጌታን በሚያመልኩበት ቦታ፣ በሚያጨበጭቡባቸው ወይም ለምስጋና አነስተኛ መሣሪያዎችን የሚጠቀሙባቸው ቦታዎች ብዙ አጋንንትን አይስቡም። ብዙ አዳራሾችን ሳያስታውቁ ከተቆጣጠሩ በኋላ አሁን ደግሞ አዲስ አዝማሚያ መጥቷል።
በቅርቡ በኢንተርኔትና በየቦታው እየተሰማ ያለ አንድ "ሳቢ መዝሙር" እየሰማችሁ ይሆናል። በ"ልሳን" ታጅቦ በኤአይ ተቀናብሮ የተዘመረ መዝሙር ነው።ሊያውም በረቀቀ ሙዚቃ የተዋዛ። እሱን እየሰማችሁ እያለ ምን ተሰማችሁ? የሚያሳክክ ነው ወይንስ የሚያስደስት? ሰላም የማይሰጥ ከሆነ ከጨለማው መንፈስ ነው።ቅዱስ የጌታ መንፈስ በስንቱ አዘነ። ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያንና ለእኛ በ1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 14 ላይ ወደጻፈው ቃል እንሂድ። በዚያም ጳውሎስ ዛሬ በአብያተ ክርስቲያናቶቻችን እንደሚታየው፣ ለልሳን ትልቅ ቦታ በመስጠት ሌሎችን መንፈሳዊ ስጦታዎች ችላ የማለትን አደጋ እንዳለ ጠቁሞ ለቤተ ክርስቲያን አስጠንቅቋል። አሁን በልሳን የሚዘመሩ መዝሙሮችን የመፍቀድ አደጋ፣ በማይታወቅ ልሳን እና በመተት (ድግምት) መካከል ያለው ልዩነት ለማወቅ መለያው በጣም ቀጭን መሆኑ ነው። ኢየሱስን ካስከበረ ከመንፈስ ቅዱስ ነው፤ ሰው ተኮር ሆኖ ንግድ ከተጡዋጡዋፈ ግን አጋንንትን መጥሪያ መንገድ ነው። በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ አማኞች በልሳን ይናገራሉ። ፍሬጋ ነው ልዩነቱ።
ጠንቋዮች፣ መተተኞችና የጨለማው ባሕር መንግሥት ወኪሎች ግን ድግምት ይደግማሉ። ሁለቱም ድምፃቸው ይመሳሰላል። ነገር ግን ልዩነቱን መረዳት የሚችሉት መናፍስትን የመለየት ጸጋ ያላቸው ሰዎች ብቻ ናቸው።
ከፍተኛ ኃይል ያላቸው አንዳንድ የጨለማ ባሕር መንግሥት ወኪሎች በመዝሙር እንዲያገለግሉ ሲፈቀድላቸው፣ አጋንንትን ወደ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ድባብ ለመጥራት በማይታወቅ ልሳን መዘመር ውስጥ ሊሸሸጉ ይችላሉ፤ ብዙ ሰዎችም በአጋንንት ይወረራሉ። ምንም ሳያውቁ አጋንንትን ተሸክመው ከአገልግሎት ይወጣሉ። አጋንንት ወደ አንድ የአገልግሎት ድባብ ውስጥ ሲጠሩ በዚያ ድባብ ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን መንፈሳዊ ጥፋት መገመት ትችላላችሁ። እንደ ቅዱስ ሃይማኖታዊ መንፈስ ሆነው የሚሠሩ አደገኛ አጋንንትና መናፍስት አሉ። እነርሱ በጣም አደገኛና ለመለየት አስቸጋሪ ናቸው።
በእግዚአብሔር ፊት ሊያስለቅሷችሁ የሚችሉ ኃይለኛ የአምልኮ ወይም የምስጋና መዝሙሮችን ሊዘምሩ ይችላሉ። ነገር ግን ከእግዚአብሔር አይደሉም። እነዚህ መናፍስት ያሉባቸውን ሰዎች የምታውቁበት መንገድ ድብቅ ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በኃይል ያገለግላሉ፤ ነገር ግን ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ምንም ዓይነት ክርስቲያናዊ ምስክርነት የላቸውም። ዳግም የመወለድ ማስረጃ የላቸውም። የመንፈስ ፍሬ የላቸውም። ያላቸው ኃይለኛ ወይም ሲንቆረቆር ጣፋጭ ድምፅ ብቻ ነው። ቤተ ክርስቲያን ሆይ፣ ለአጋንንት አሠራር አመቺ ሁኔታ እንዳይፈጠር፣ ልንረዳው በምንችለው የሰው ቋንቋ ያልተዘመሩ መዝሙሮችን መፍቀድ የለብንም። የሚዘመረውን ሳንረዳ እንዴት አብረን እንዘምራለን? ማንኛውም ሰው በልሳን እየዘመርኩ ነው ሊል ይችላል፣ በተግባር ግን ድግምት እያደረገ ሊሆን ይችላል። ብስለት እስኪመጣ ድረስ በመረዳታችን ብቻ እንዘምር፤ በልሳን የሚዘምርም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በቤቱ ለራሱ ይታነጽበት። እንጠንቀቅ። ዲያብሎስ ለመጨረሻው ዘመን መንፈሳዊ ጥፋት እንዲያመጡ ብዙ ወኪሎቹን ወደ አብያተ ክርስቲያናት ልኳል። አሁንም ተጠንቀቁ። ዘመኑ ፈታኝ ነው። "ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ" ጊዜው ባያጥርስ የተመረጡት እንኳ እስኪስቱ ድረስ ይታለሉ ነበር።
#ማራናታ!
ለክብሩ የመጨረሻ ዘመን የመንፈስ ቅዱስ ዝናብ ናፋቂ ሰው ድምፅ!
Pro Gold
👁 6 🔁 0 Publication date:
10 Apr, 14:03

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ታስፈልገኛለህ!
ኃጢአት በደሌን በመስቀል ላይ ጠርቀህ አስወግደህ እድፈቴን አጥበህ አነጻኸኝ። ልጅ አረከኝ። አድርገህልኛልና ለዘላለም አመሰግንሃለው። ጌታ ሆይ ያላንተ አልችልም። አመስግኑ ቸር ነውና ምህረቱ ለዘላለም!
Pro Gold
👁 9 🔁 0 Publication date:
07 Apr, 08:06

ትህትና በተግባር ታየ። በኢየሱስ ደም አምኖ ከኃጢአቱ የታጠበ ሁሉ ዳነ። የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያነጻል። በደምህ አምነን ነጽተናል... ጌታ ሆይ ተመስገን!
Pro Gold
👁 10 🔁 0 Publication date:
04 Apr, 11:48

በክርስቶስ ኢየሱስ ስም እስራት ተበጣጠሰ!
ወጥመድ ተሰበረ! ቅዱሳን አመለጡ!
Pro Gold
👁 11 🔁 0 Publication date:
02 Apr, 18:10

ንጉሱ አስቴርን ይህን ጥያቄ ሶስት ጊዜ ደጋግሞ ጠይቋታል "... “ንግሥት አስቴር ሆይ፤ የምትለምኚው ምንድን ነው? ይሰጥሻል፤ የምትጠይቂውስ ምንድን ነው? እስከ መንግሥቴ እኩሌታ እንኳ ቢሆን ይደረግልሻል” አላት።
...
ከዚያም ንግሥት አስቴር እንዲህ ስትል መለሰች፤ “ንጉሥ ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ አግኝቼና ግርማዊነትህን ደስ የሚያሰኝ ከሆነ፣ ሕይወቴን ታደጋት፤ ልመናዬ ይህ ነው፤ ሕዝቤን አትርፍ፤ ጥያቄዬም ይኸው ነው። እኔና ሕዝቤ ለጥፋት፣ ለዕርድና ለመደምሰስ ተሸጠናልና። ወንዶችና ሴቶች ባሮች ለመሆን የተሸጥን ቢሆን ኖሮ፣ ዝም ባልሁ ነበር፤ ምክንያቱም እንዲህ ያለው ጭንቀት ንጉሡን ለማስቸገር የሚበቃ አይደለም።”
...
ስለዚህ ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሐማን ሰቀሉት፤ ከዚያም የንጉሡ ቍጣ በረደ። (አስቴር 7፥2-4፣ 10)
• ምንም እንኳ አስቴር በንጉሱ ፊት ሞገስ ያገኘች ቢሆንም ቤተ-መንግስት ውስጥ ብቸኛ ነበረች። ለእርስዋ ድምጽ የሚሰጣት ሰው አልነበረም። ልዑል እግዚአብሔር ግን ከእርስዋ ጋር ነበር። ጌታ ድምጽ ሆናት። ያ ብቻ ሁለመናዋን ቀየረው።
ሐማ መርዶክዮስን ለማሰቀል ደሞ የአይሁድን ህዝብ ለማስጨፍጨፍ ሲሸርብ ሲያደባ ሲያድም ሲያነሳሳ ክፋት እየጠነሰሰ ከርሞ ባዘጋጀው ወጥመድ ተያዘ። ጠላቶቻችሁ ለእናንተ ባዘጋጁት ወጥመድ ተያዙ! በቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ገቡ! ስራቸው ይፍረስ!
የጌታን ፍጹም ፍቃድ ማስቀየር የሚችል ማንም የለም።
Pro Gold
👁 7 🔁 0
Russian

