ከጀልባዎቹም መካከል የስምዖን ወደ ነበረችው ገብቶ፣ ከምድር ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ለመነው፤...
ከጀልባዎቹም መካከል የስምዖን ወደ ነበረችው ገብቶ፣ ከምድር ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ለመነው፤ ከዚያም ጀልባዋ ላይ ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ጀመር።
ሉቃስ 5÷3
.
.
.
ሌሊቱን ሙሉ ባህር ስታካልል አድራ ባዶነትን ታቅፋ ዳር የያዘች ባዶ ጀልባ ውስጥ ምን ትሰራለህ ጌታ ሆይ???
መለመንህስ እንዴት ያለ ቅኔ ነው?
በስሱ ማዕበል የምትወዛወዝ ጀልባ ውስጥ ሆነህ ስለ ምን አስተማርካቸው ያን ቀን?
እኔማ
ይታየኛል ትሁት መልክህ
ይሰማኛል ሰላም ድምጽህ
በጌንሳሬጥ ጀልባ ተውሰህ
ይሰማኛል ስታስተምር ይታየኛል ህዝብህ ሲያይህ
ከጀልባዋ ስትወርድ አለት አስከትለህ
በመንደሮች ስትዞር
ስትራራ ስትምር
ስትሸከም ደዌ ቁስል
ህማም ስቃይ ስትቀበል
ስታዘግም ወደ መስቀል
ይታየኛል ትሁት መልክህ
ይሰማኛል ሰላም ድምጽህ
አይሃለሁ ተንቀህ
ሀጢያተኞች አስከትለህ
ደግሞም አይሃለሁ በየአውራጃው ስትወርድ
ከገሊላ ቅፍርናሆም ሰማርያ ስትሄድ
አይሃለው ቀራጭ ስትወድ
አመንዝራን ስትምር ሳትፈርድ
የተጣሉን ስታይ ስትወድ
ያመኑህን ስትጋርድ
ይታየኛል ትሁት መልክህ
ይሰማኛል ሰላም ድምጽህ
ይሰማኛል መጠላትህ
አየሁህ ወደህ
አየሁህ ተንቀህ
አይሃለሁ ከብረህ!
113
0
0
10
Similar channels




