Kalon

@penchantforkalonandmetanoia
Latest publications
Publication date:
02 Sep, 17:16
በሃሳብም በአካልም በስልክም እየሄድን ጥቂት ጸጥ እንላለን ሌላ የሚ'ተረብ ሰው እስኪመጣ። እኔ ደግሞ በመስኮት በኩል ወጥቼ የማላስበው ሃሳብ የማልበርበት ስፍራ የማልጠይቀው ጥያቄ ዞር ብዬ የማላየው ትዝታ የለም። የሚገርማችሁ ነገር የአዲስ አበባ ሰው አይተኛም! እግዚኦ! አ.አ.ን በሳይነጋው በሰርቢስ ስናካልላት ታዲያ፡ የማለዳ ዝናብ ያልበገረው ግድንግድ የታክሲ ሰልፍ አያለሁ። ሀብታም በመኪናው ከብርድና ከሰልፍ ቢድንም ጓርፍ ሲተናነቀው አያለሁ። ሰው ይተማል። ማታ ስንመለስ ደግሞ በጥላዋ ራሳን ልጇንና በቆሎ የምትጠብስበትን እሳት ከልላ መንገድ ዳር የተቀመጠች እናት አያለሁ። ሁለት አቅመ አዳምና ሄዋን በቆሎ ገዝተው እየጋጡ በሁዲ ያዘግማሉ። በዚህ ኑሮ ውድነት ማን እንደሚበላላቸው የማይገባኝ የስጋና የቁርጥ ቤት ሼፎች መስኮት ላይ ሆነው ሁሌ እንደከተፉ ነው።
ትራፊኩ ሲዘጋጋ አንድ የሀብታም መኪና ከጎኔ ይገተራል። አጓንብሼ አያለሁ። ተለቅ ያለች ሴት የምትነዳላት አንዲት ባለቢጫ ጸጉር ኮረዳ ሜካፗን እየሰራች ነው። ህጻናት ከጀርባ ወንበር ቡዝዝ ብለው በመስኮት ወደ ውጪ ያያሉ።
ለአመታት አጎበር የለበሱ ህንጻዎች አሁንም በጀት እየጠበቁ ነው። የኮሪደር ልማቱ ሊሸፍናቸው ያልቻላቸው የኮብል ውስጥ የድህነት ቤቶች አልፈው አልፈው ብቅ ይላሉ። አንዳንዴ ግን የምሰማው መዝሙር አንዳንድ ስንኞች በሁኔታዬ ጋር ልክክ ይሉና ትኩረቴን ከማየው አንስተው ወዳላየሀት ይሸኙኛል።
ታዲያ እንደለመደብኝ ማንም አይሰማኝም ብዬ ከኤርፎኔ ጋር አ'ብሬ የጆንን መዝሙር ሳንጎረጉር የአንዲት ዶክተር ወይዘሮ ጆሮ ውስጥ ገባሁኝ። ከጀርባዬ ነክታ "በጌታ ነሽ?" አለችኝ አይቼባት የማላውቀው ፈገግታ ውጧት (ወይ የዳነ ሰው❤️!) አዎ ነበር መልሴ። ተያማ ወዳጅነታችን እስከ ሰማይም ሆነ አይደል? ከድሮም ሰፈራችን አንድ አካባቢ ነበር። ዶክተር ቁጥብነቷ አውልቃ ከማታውቀው መነጽር ጋር ተባብሮ አስተዋይነቷን ያሳብቅባታል። እነሱ ቸርች አንድ እሁድ አብረን ለመሄድ አቅደናል። አትስጉ international church አይደለም😁። አሁን ህብረት እያደረኩበት ያለው ቤተ-ክርስቲያን ምንም እንኳ international church ባይሆንም ስነግራት ፊቷ ላይ ጥሩ እንዳልተሰማት አንብቢያለሁ። ከዛማ በሌላኛው ቀን ሌሎችንም የሰርቪሳችን አማኞች ጠቆም ጠቆም አደረገችኝ። ይገርማል አብዛኞቹ ጭራሽ ያልገመትኳቸው ናቸው። ሁሉም ነገራችን "ኧረ የህይወት ያለህ🗣" ያስብላል። እኔና እሷ ራሱ ከቀናት በኃላ ነው የተዋወቅነው። የማያስታውቅ ክርስትና!
ጸጥታዋ ጊዜ እየጠበቀች ጃዥ ትለናለች።
ጋሽ ሙሄ ታዲያ ጸጥታውን ሰበር ያደርጉና
"በነገራችን ላይ ይህንን ሉፍታንዛ መንዳት ቀላል እንዳይመስላችሁ! ጋሽ ረታ ብቻ ናቸው የሚዘውሩት ከፕሌን አይተናነስም..." በማለት ሹፌራችንን ወደ እኛ ዞረው ያሞጋግሷቸዋል። ከጀርባ ያለን ወጣቶችም ካጎነበስንበት ስልክ ቀና ቀና ብለን "እውነት ነው..." በማለት ይጨማምሩላቸዋል። ጋሽ ረታ ይሄኔ ታዲያ ጀነን ብለው መሪውን ዞር ዞር ያደርጉታል።
ጋሽ ሙሄ ስልክ ሲጓረጉሩ አይቻቸው አላውቅም ለዛ ይሆናል የአንስቴዢያ ሙያ ሳይገድባቸው እንዲህ ተጫዋች የሆኑት። ይሄ ስልክ የሚሉት ጉድ ለዛችንን ነጠቀን እኮ። በነገራችን ላይ ጋሽ ሙሄ ትናትና ጡረታ ወጡ😭። ጭርታው ከወዲሁ ያስፈራል። ዛሬ ጥዋት ሁላችንም በየተራ አቅፈናቸው መልካም እየተመኘንላቸው ቻው ተባባልን።
በዓልን ከእኛ ጋር እንደሚያከብሩ ቃል ገብተውልን ተለያየን። ሰርቪስ ውስጥ እንድፈላሰፍ የሚረዱኝ ሞገሳም አባ ወራ ከዚህ በኃላ የሉም።
ሁሌ ይልፉ አይባልም አመሻሻቸውን ከቤተሰባቸው ጋር ፈታ ይበሉ ባይሆን።
ጥረቱንና ግረቱን ተወጡት ማለት ነው።
God, i am still counting my blessings!
All of you've done in my life
The more that i look in the details
The more of your goodness i find...
ህይወት ይብዛልን🤍✨
👁 69 👍 16 💬 25 🔁 1 Publication date:
02 Sep, 17:16
እኔ ምለው ለመኖር ግዴታ መስራት አለብን?
ማለቴ ይቺን ኑሮ ለማግኘት ይህን ሁሉ ዋጋ መክፈል ግድ መሆን ነበረበት? ስራ ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ ይሄ ነው ጥያቄዬ። "ጥረሽ ግረሽ ብይ" እንደው አልተባለ። ብንግር እንኳ ቢያንስ ቢያንስ ምግብና መኖሪያ በነጻ ሊሆንልን ይገባ ነበር🙂↔️። አዲስ አበባ ግን ጥረቱም ግረቱም ከበድ ይላል በእውነት።
ለማንኛውም😁 እህሳ እናንተሳ እንደምንድን ናችሁ? ክረምቱ እንዴት እንዴት እያደረጋችሁ ነው እናንተዬ? የአዲስ አበባዋ ጸሃይ ዝናብ አላፈናፍን ብሏት ደመና ውስጥ ተቀብራ ልትሻግት ነው እኮ!
ስንት ቀን አለፋት ከወጣች? ለነገሩ ሰሞኑን ለሰላምታ ያህል ብቅ እያለች ነው። አዲሱ አመትም ደርስኩ እያለ ነው። ጉድ ነው መቼም የጊዜው ነገር እኔ ማስታወሻወቼ ላይ 2017ን አየረሳሁ በ2016 እየጻፍኩ መደለዝ ያቆምኩት ራሱ ከጥቂት ወራት በፊት ነው። ድሮ ልጅ እያለሁ ለበዓል ለበዓል ልብስና ጫማ ስለሚገዛልኝ ነው መሰለኝ በዓል ቶሎ ቶሎ አይደርስልኝም ነበር። የደስታ ቀን ረዥም ነው ይባል የለ። ይሄ ግቢ ያላስረሳኝና ያላፋጠነብኝ ነገር የለም። በዓል በወጉ ካከበርኩ ድፍን አራት አመት ሞላኝ። ቀሪዎቹን ይባርክልኝ እንጂ ተይ በኃላ በዓል የማክበር እቅድ አለኝ። ቀስ ቀስ እያሉ እንዲመጡ ማለት ነው🙃።
እየሆነ ያለው ይሁንና፡ ከአዲሱ ስራዬ የወደድኩት አንዱ ነገር የservice ውስጥ ወጋቸውን ነው። ሹፌራችን ጋሽ ረታ ከየሰፈራችን የሚያነሱበት የየራሳችን ሰዓት አለን። በተባሉት ሰዓት የተባሉበት ቦታ መገኘት ትልቁ የሉፍታንዛችን (የሰርቪሳችን) መተዳደሪያ ደምብ ነው። ለማርፈድ የሚሆን ምክንያት የለንም። ዘነበ፣ መብረቅ ጣለ፣ ትራፊክ አስቸገረኝ...የሚሉ ምክንያቶች "ተልካሻ" ናቸው። ስለዚህ ሐዋሳ አሳስባኝ የማታውቀውን የብርድ ልብሶች አሰባሰባስቤና ሻንጣዬ ውስጥ ያለኝን ሹራብ ሁሉ ደራርቤ በጥዋት ከቤት እወጣና ሉፍታንዛችን እኔን ብሎ ወደሚቆምበት አደባባይ አቀናለሁ። ብርዱን ላለመስማት የጆሮ ማዳመጫ የግድ ነው። ከዛም በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ። ጋሽ ረታ ወደ 70ዎቹ እየገሰገሱ ያሉ እርጋታን በዝምታ ላይ የተከናነቡ ደርባባ ሹፌር ናቸው። እያከነፈ ከሚወስደን ወጠጤ(ወጣት) የእሳቸው ቀስ ብሎ መንዳት ቶሎ ያደርሰናል። ታዲያ ከሌላ ሰፈር ያገኟቸውን ሰራተኞች እየለቃቀሙ ልክ 12:50 ሲል እኔው ጋ ይደርሱልኛል። ጮክ ብዬ እልልልል እያልኩ (በሆዴ) እገባለሁ። ሉፍታንዛችን ሙቀት አላት። ጋቢና የጋሽ ተስፋዬ (የፖርኪንግ ሰራተኛችን) ዙፋን ነው። እሳቸውም ጀነን ብለው ፊት ፊታቸውን በተመስጦ ጀርባቸውን በስፖኪዮ እያዩ ከጋሽ ረታ ጋር በዝምታ ይነዳሉ። ጋሽ ተስፋዬ ጡረታ የወጡ የቀድሞ ወታደር ናቸው ኮፍያና የሳምሶናይት ቦርሳ የማይቀር አለባበሳቸው ነው። ከጀርባ ያለነው ወጣቶች የሚረባውንም ማይረባውንም ያጉተመትማሉ እኔ በዝምታ background በመሆን እተባበራለሁ። ትንሽ እንደሄድን አንድ አድራጊያችን ጋሽ ሙሄ ጋር እንደርሳለን። ጋሽ ሙሄ አንስቴቲስት ናቸው። ነጭ ጸጉራቸው ከአንደበተ ርቱዕነታቸው ጋር ተጃምሎ የሉፍታንዛችን ውበት አድርጓቸዋል። እሳቸው ከገቡ በኃላ አንዳችንም ዝም ማለት አንችልም። "የታለች ያቺ ትንሿ ልጅ🕵️♂️" ብለው በአይናቸው ይፈልጉኛል። አቤት ደስ ሲለኝ። "አለሁ ጋሽ ሙሄ" ብዬ ከነጋ የመጀመሪያ ፈገግታየን እለግሳለሁ። "እየለመድሽ ነው? ማን አስቸገረ ንገሪኝ ለኔ? አይዞሽ..." ይሉኛል በየማለዳው። ከዛ ከነ ጋሽ ረታ ጋር መተራረብና የጃንሆይን ጊዜ እያስታወሱ መቀላለድ ይጀምራሉ (እኔ የሚመቸኝ scene ተጀመረ ማለት ነው)። ጋሽ ሙሄ ከገቡ በኃላ ጋሽ ረታ እንኳ ዝም ማለት አይችሉም።
መገናኛ ልንደርስ አካባቢ ጋሽ ሙሄ ጉነጣቸውን ይጀምራሉ "ጋሽ ተስፋዬ እኮ በዚህ አካባቢ 1000 ካሬ ነበራቸው ወታደራዊው መንግስት መራው እንጂ" ይላሉ ፎቆ ጥቅጥቅ ብሎ የተሰራበትን አቅጣጫ እየጠቆሙ😁።
"ጃንሆይ ስር ስር ሲሉ ነዋ😁" ጋሽ ረታ ናቸው እንዲህ ሚሉት። ያው እንስቃለን እኛ።
"ምንም ቢሆን የእስክንድር ደስታ ወዳጅ ነበርኩ።" ይላሉ ጋሽ ተስፋዬ በኩራት።
"እውነት ነው እሳቸውማ ጀግና የባህር አዛዥ ነበሩ። መኮንን ደስታም ቢሆኑ ለቀሚስ ሲሉ ተኮላሹ እንጂ እሳቸውም ጎበዝ ነበሩ።"
ይላሉ ጋሽ ሙሄ ነጭ ጸጉራቸው ውስጥ ትዝታን በእጃቸው እያሻሹ።
"ተናኘ እኮ እስክንድርን ማንገስ ትፈልግ ነበር። እሳቸው እንቢ አሉ እንጂ። ደግሞ ብታይ ገና በ90 አመታቸው ነው የተቀጩት በወታደሩ መንግስት።" ይላሉ ጋሽ ተስፋዬ እስክንድር በ90 አመት መሞታቸው እያንገበገባቸው። ጋሽ ሙሄ ወደኔ ዞር ይሉና "ሰው ስንት ቢኖር ይበቃዋል ትያለሽ የኔ ልጅ?" ይሉኛል። ይህንን ከባባባድድ ጥያቄ ምን ብዬ ልመልስ እያልኩ እንዳፈጠጥኩ የነ ጋሽ ረታ ወሬ ጠልፎ ከእኔ መልስ ዞር ያደርጋቸዋል። እፎይይይ እላለሁ። ጥያቄውን ከባድ ያደረገው 70ና 60 አካባቢ ላሉ ሰዎች የሚመለስ መሆኑ ነው። የእኩዮሽ ጭውውት አይደለም።
"ለምን ወደ ኬንያ አልሸሹም ግን እሳቸው?" የጋሽ ረታ ጥያቄ ነው።
"አይይይ ያኔ ነውር ነበራ ሽትተ! መጋፈጥ ነው ጀግንነት😁" ብለው ይመልሳሉ ጋሽ ተስፋዬ እየሳቁ።
"አይ ጊዜ" በምትል አይነት ጸጥታ ትንሽ ካዘገምን በኋላ ሌሎች ሰራተኞች ቆመው የሚጠብቁን ቦታ ላይ እንደርሳለን። "እዚህ ጋር የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አሉን ጋሽ ረታ" ብለው ያስታውሷቸዋል ጋሽ ሙሄ።
ከሰሞኑ አንደኛው ቀን ላይ የአሸንዳው ጉንጉን ያላረጀባት አንዲት ነርስ በሽፎን ተከስተች።
"እዩአት የ17 አመት ልጃገረድ መስላ ስትመጣ አቤት አቤት...ቱቱ ከአይን ያውጣሽ ያ ዩኒፎርምማ ጉድ ሰርቶሽ ነው እኮ የከረመው😁" ብለው ፊቷን የለ አኳሏን ጥርስ በጥርስ ያደርጓታል። እኛም አስተያየታችንን እናክላለን። ጉነጣው እንዳይቀርባቸው ደግሞ
"አይንም በኩል ያምራል ጥርስም
በንቅሳት፣
ትንሽ አፍንጫ ነው ይቺን ልጅ ያነሳት😁"
ብለው በግጥም ነገር ጣል ያደርጉላታል። እንዲህ እያዋዛን እነሱን ጨምረን ጉዞው ይቀጥላል። ወይ አዲስ አበባ ይሄው ስንት ቀኔ በአንድ አይነት መንገድ መመላለስ ከጀመርኩ ግን በየጥዋቱ የማላውቀው ህንጻ ይታየኛል። ምን የማትለመድ ጉድ ናት? ቀን በቀን ሰው የማይኖርበት ህንጻ ማብቀል... ኤዲያ። ህዝቡ ዳር ዳሩን ሰፍሮ ይሰቃያል መሃሉ ባዶውን ያድራል። ትጨንቃለች።
👁 64 👍 8 💬 0 🔁 0 Publication date:
23 Aug, 06:39
Look again to the love of the savior, and behold that love which constrains you to live no more to yourself, but to him that died for you and rose again.
look again!
“በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።”
— 2ኛ ቆሮ 5፥15
👁 139 👍 12 💬 0 🔁 0 Publication date:
21 Aug, 14:47
August 01/2025
መኖር ስሰስት ማወቅ ስናፍቅ
ሰላም ስር ስር ስል ጊዜን ስወ'ርቅ
ቀኔን ስቆጥር መሸ ይንጋ እያልኩ
እንደሰጠኸኝ እንዳልተነገርኩ
ተስፋን ነጥቀው የሸኙኝን ላለመምሰል ባከንኩ
ባከንኩ በረከት አባከንኩ ለስንፍና ተንበረከኩ
የቸርከኝን ችሬ ለቀኩ
ፍቅርህማ ሸፋኝ ጠበል
ጉያህማ ለኔ ጠለል
ልቤን ላድን ብቃብዝም
ከመ'ቧጨር አልተረፍኩም
ስፈርድ ስመስላቸው ስቸር ባዶ ስቀር
እረስቼ አረፍኩት ስሜ ማ እንደነበር
ማን ነኝ? ማን ሆንኩ?
እሷን መሰልኩ? እሱን አከልኩ?
እስክጠፋ ተደናበርኩ
ከማህሌ ታጣሁ እስከ ደጄ አዘንኩ
ጥጌን ነካሁ መልኬን አየሁ
መልከዓልኬን እመስላለሁ
መላላኬን አክላለሁ
ግን እንደው ግን
"እጣን አለሁ" ያልኩህ ውበቴ
"ቅዱስ" ያልከኝ መስታወቴ
ህያው ብዬ ያቃጠልኩት
ልረድ ብዬ ያጋደምኩት
ጽዱቅ ያልከው ሰውነቴ
ደስታህ ነው ወይ መስዋዕቴ?
የነሃሴ ድምጾች✍
👁 151 👍 8 💬 0 🔁 0 Publication date:
20 Aug, 05:26
እኛ ራሳችን ከእግዚአብሔር በተቀበልነው መጽናናት፣ በመከራ ያሉትን ማጽናናት እንድንችል፣ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።
2 ቆሮንቶስ 1÷4 (አ.መ.ት.)
👁 187 👍 13 💬 0 🔁 2 Publication date:
17 Aug, 08:00
የተከበበ በማይጠጣ
በአለም ያለ ሰው ኢየሱስን ያጣ
በጀልባ እንደጠፋ ውቂያኖስ ላይ
ኢየሱስ የሌለው ሰው እሱ አይደል ወይ
ተበልቶ ተጠጥቶ የለም እርካታ
ኑሮ ማለት ሀሩር ከሌለው ጌታ!!!
- ቤኪ
👁 189 👍 16 💬 0 🔁 1 Publication date:
14 Aug, 03:34
Remember, it is not your weakness that will get in the way of God's working through you, but your delusions of strength!!!
👁 207 👍 9 💬 0 🔁 0