ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምድር ላይ በስጋ ወራት እየተምላለሰ ሳለ እንዲህ አለ ...
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምድር ላይ በስጋ ወራት እየተምላለሰ ሳለ እንዲህ አለ
“አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያሳስባችኋል።” (ዮሐንስ 14፥26)
ልክ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበትን ዋነኛ ተልዕኮ (የዲያብሎስን ስራ ማፍረስ) ከፈጸመ በኋላ ተመልሶ ወደ ገናና ክብሩ ወደ አብ ከሄደ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ወደ ምድር መጣ። አሁን በአለም ሁሉ እየሰራ ያለው መንፈስ ቅዱስ ነው። ምን ይሄ ብቻ አሁን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከመሆኑ አልፎ በውስጣችን አለ፤ በእኛ ውስጥ አደረ። እለት እለት ይሞላናል፤ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ ያስተምረናል።
እርሱ ከኢየሱስ አስተምህሮም ሆነ ተልዕኮ የሚቃረን ትምህርት ያስተምረንም። ልክ ጌታ አብ ሲያደርግ ያየውን ሲያደርግ እንደነበር ሁሉ መንፈስ ቅዱስም ክርስቶስ ሲሰራ እንደነበር በእኛ ውስጥ አድሮ ይሰራል። ወንጌልን በዳኑ ቅዱሳን ውስጥ ሆኖ ይሰብካል።
በክርስቶስ የሚያምኑትን አማኞች ያበረታታል፣ ያጽናናል፣ ያጸናል፣ ይፈውሳል፣ ይረዳቸዋል፣ ወደ ኢየሱስ ይመራቸዋል፣ ቃሉን እንዲያስታውሱ ያደርጋቸዋል፣ በኃጢያት ህይወት ውስጥ እንዳይቀጥሉ ይወቅሳቸዋል፣ ያሳድጋቸዋል፣ አካሄዳቸውን ከኢየሱስ ጋር እንዲያደርጉ ያደርጋቸዋል፣ ሌላ በጣም ብዙ ብዙ ነገር ያደርግላቸዋል። ለእኔም መንፈስ ቅዱስ ልገልጻቸው የማልችላቸው በርካታ ነገሮች አድርጎልኛል። ምንም እንኳን በኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን ልምምድ እና አማኙ ህዝብ ልቤ ቢያዝንም እርሱ መንፈስ ቅዱስ ግን ያን ሁላ ተንኮል እና ክፋት አልፎ እየሰራ ይገኛል። የተባረክ ነህ!
እኔማ አለ መንፈስ ቅዱስ ምንም ነገር ማድረግ ሆነ መሆን አልችልም። እስከዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ ምድር ሳገለግል ያለ ማንም እርዳታ እየባረከ፤ እየረዳኝ፤ እየመራኝ ያለው እርሱ ብቻ ነው። በሕይወቴ ውስጥ ትልቁን ቦታ የያዘው መንፈስ ቅዱስ ነው። ውዴ ሆይ ተባረክልኝ!
ትልቁ ሪቫይቫል ድንቅ እና ተዓምራት ከማድረግ ያለፈ ሲሆን ይኸውም ነፍሳትን ለኢየሱስ መማረክ ነው። ይሄንንም ስራ ፊተኛ ሆኖ እየሰራ ያለው መንፈስ ቅዱስ ነው። አሁንም እንደገና ለጉድ ይጠቀምብናል… በሰዎች ይሁንታ ወይም አሜንታ ሳይሆን በልዑል ሉዓላዊ ምርጫ… ሃሌሉያ!!
Z Anointed Gold
Similar channels
Russian
