ጌታ ኢየሱስ የሞተላቸው ነብሳት እርሱን ሳያውቁ ወደ ሞት መውረዳቸውን አይቶ ያዝናል። ለራሳችሁ ...
ጌታ ኢየሱስ የሞተላቸው ነብሳት እርሱን ሳያውቁ ወደ ሞት መውረዳቸውን አይቶ ያዝናል። ለራሳችሁ ከዳናችሁ በኋላ ለሚጠፉት ሕይወቶች እንዴት ግድ አይላችሁም? ጠገባችሁ፤ ቀያይራችሁ ለበሳችሁ፤ ቀያይራችሁ ነዳችሁ…። መልካም ሆንላችሁ። እናንተ ግን ነገ ወደ ፍርስራሽ ክምር የሚቀየር ፎቅ እና ግንብ ለመስራት ባተላችሁ። ስሙ ፈራሽ እኮ ነው። ጠፊ ነው! ‘ቁሳቁስ ማጋበስ መብቴ ነው፤ ውድድሩን ላጡዋጡፈው፤ ፉክክር ያምርብኛል፣ ዋና እኔ ነኝ… መለኪያው እኔ ነኝ፣ ሐብቱንም ዝናውንም ስልጣኑንም ልቆናጠጠው፣ እኔ ከማንም እበልጣለው… እኔ ነኝ ትክክል…’ እያላችሁ በእኔነት ስውር ስፍ ተሰፍቶ ልባችሁ አበጠ።
አትመለሱም? ምነው ልባችሁ ልክ በጋለ ብረት ምጣት እንደተጠበሰ ስጋ ሆነ፤ ትንሽ አይሰማችሁም? የበራላቸውን እየገፋችሁ በሞቅታ እና ስቅታ ያጀቡዋችሁን “ቲፎዞ” ብቻ ማስተባበር ሆነ በቃ ስራችሁ? የየራሳችሁን ሎሌ መልምሉ ያላችሁ ማነው? አይናችሁ ይብራ! ስለ ማን እንደማወራ ይገባችኋል። “ወደ እርድ የሚነዱትን አድን፤ ለሞት የተዘጋጁትን ታደግ” ተብለናል። ለወንጌል ተነሱ!
“ፍርድ ከቤት ይጀምራል!” ስሙ እነ ቀልጣፋ ነጋዴዎች፤ ጌታ በመንፈሱ ጅራፍ እየገረፈ ከቤቱ ያስወጣችኋል። ህዝቡን የበከላችሁበት ዘመን አበቃ።
ነገሮች ግልብጥብጣቸውን ሳይወጡ አስተውላችሁ ወንጌል ብትሰሩ መልካም ነው። ምክንያት አታብዙ ወንጌል ስሩ። “በጊዜውም አለጊዜውም ወንጌል ስበክ” አትሞዳሞድ። ዘመን አልቋል። ይሄ ሁላ ዘመን ገመገምክ፤ ሰለልክ፤ ተወያየህ… ምን አዲስ ነገር አመጣህ። ልበ-ደንዳና፤ አይነ-ደረቅ ትውልድ ነው ያፈራኸው። በውስጡ አለም ተሰግስጋ በፍቅርዋ የሰከረ ትውልድ አፈራህ። ይሄ ነው የተሰጠህ ኃላፊነት? ለእያንዳንዱ እንደየስራው ሊከፍል ዋጋው በእጁ ነው። #ኢየሱስ_እየመጣ_ነው!
Similar channels
Russian
