ጊዜው የምርጫ ነው ይላሉ፤ ብዙ ለህይወት የሚሆን ምርጫ ያለ ይመስል። ቀለል አርገህ ኑር፣ አታካ...
ጊዜው የምርጫ ነው ይላሉ፤ ብዙ ለህይወት የሚሆን ምርጫ ያለ ይመስል። ቀለል አርገህ ኑር፣ አታካብድ፣ አታክርር፤ ቀስ ብሎ ይደርሳል፥ ይባላል። ዘለዓለም ጊዜ ያለ ይመስል። ነገሩ ግን እንዲህ የሚቃለል አይደለም። ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ እድሜያችንን መቁጠር አስተምረን። (መዝ 90:12 አ.መ.ት) ተብሎ ተፅፏል፣ የተወሰኑ ቀናት እንዳሉ ለማመልከት። ምርጨዎቹም ጥቂት፥ እንዲሁም ሁለት ብቻ ናቸው፤ አንዱ ባንዱ ላይ የማይደራረብ፥ የማይደባልቅ። እንግዲህ ዛሬ ህይወትን እንምረጥ፤ እንደሚገባም በድርጊት እየገለጥን እንኑረው። መሐል ሰፋሪ መሆን አይቻልምና፥ እኛ ዛሬ ልባችንን ያዘጋጀነው ለምን ይሆን፤ “ዕዝራ ግን የእግዚአብሔርን ሕግ ይፈልግና ያደርግ ዘንድ፥ ለእስራኤልም ሥርዓትንና ፍርድን ያስተምር ዘንድ ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።”
ዘላለም ማሞ
98
0
0
14
Similar channels





